መግቢያ

ሳድስ የንባብ መጻፊያ ፕሮግራም ነው፤ ለምሳሌ እንደ ኖትፓድ (Notepad)። ሳድስ ግን ለኢትዮጵያ ፊደል አመቺ ስለሆነ፥ ዩንኮድን በሚከተል በኢትዮጵያ ፊደል ፎንት በቀላሉ ንባባዊ ሰነድ ለመጻፍና ለማዘጋጀት ያስችላል። በተለይ በዩንኮድ ላይ የተመሠረተ ዌብ ገጽ ለመንደፍ፥ እንዲሁም በኢንተርነት የሚጓዝ መልክት ለመጻፍ ሁነኛ መንገድ ነው። ሳድስ የተጻፈው ባጃቫ የፕሮግራም መጻፊያ ቋንቋ ነው። ሳድስ የሚከተሉት ክፍሎች አሉት።

  • የኢትዮጵያ ፊደል ዩንኮድ ፎንት፤
  • የኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት። የኢትዮጵያ ፊደል መጻፊያ ሥርዓት።
  • ንባባዊ ሰነድ ማተሚያ፤
  • ካንድ ወይም ካንድ በላይ ንባባዊ ሰነድ መክፈቻና መጻፊያ፤
  • ንባባዊ ሰነድ በልዩ ልዩ የፋይል ይዘት መልክ መጻፊያ። ለምሳሌ፦ የጠራ ንባብ ፥ ዩ/ቲ/ኤፍ-8 (UTF-8) እና የጠራ ዩንኮድ።
  • ከሰነድ ውስጥ፥ ቃላት ወይም ሐረግ አስሶ የማግኛ መንገድ፤
  • ፎንት መለወጫ፥ የፎንትን መጠን መቀየሪያ፤
  • ያማርኛና የእንግሊዘኛ መመሪያ ሜንዩ፤
  • ያማርኛና የእንግሊዘኛ ረዳት ክፍል፤
  • ለልዩ ልዩ ቋንቋዎች በቀላሉ ተዛማጅ፤
  • ምሳሌዎች፤


ግዳጅ

የኸን ፕሮግራም ያለምንም ችግር ለማስነሳትና ሥራዎችን ለማከናወን ቢያንስ ይህ ሁኔታ መሟላት አለበት። JRE 1.4 (Java Running Enbironment) ወይም J2SE 1.4 (Java Software Development Kit) ሲሰትሙ ላይ በቅድሚያ መተከል አለበት።


ለፕሮግራም ጸሀፊዎች

የሳድስ source code በsrc መኅደር ሥር ይገኛል። ፕሮግራሙ የተጻፈው J2SE 1.4 በመጠቀም ነው። ከያንዳንዱ ፕሮግራም አጭር ማብራሪያ ስለተጨመረ ፕሮግራሙን በቅርብ ለመረዳት ያንን ይመልከቱ።


ምስጋና

ሳድስን ለመጻፍ የረዱኝ አያሌ ነገሮች ቢኖሩም በተለይ ሰፊ የርዳት ምንጭ ከሆኑኝ መካከል የሰዊንግ ፕሮጀክት ምሳሌዎች ይገኛሉ። ለዚህ የስዊንግ ፕሮጀክት አባላትን በሰፊው ላመሰግን እወዳለሁ። ከተጠቀሙኳቸው መጻህፍት መካከል በከፍተኛ ደረጃ የረዳኝ ጃቫ ስዊንግ (Java Swing) ነው። የመጽሀፉ ደራሲዎች ሮብርት ኤክስተን፥ ማርክ ሎይና ዴቭ ውድ ነቸው። የከበረ ምስጋና ለነሱ።





abass alamnehe
Copyright © 2002 Senamirmir Project